
Ethioh health hub
ስልተ አካላት/Body systems
ሁሉም ስልቶች በአማራኛ ተቃኝተዋል/ All the systems are dealt in Amharic
ስልተ ናላ የአካላችን ንጉስ ነው። እኛ የተረዳናቸውም ያልተረዳናቸውም በአካል ውስጥ የሚፈጠሩ ክስተቶች በሙሉ ትእዘዛትን የሚቀበሉት ከዚህ ስልት ነው።
ስልተ ፍሰት ኩላሊትን እና የሽንት መፈጠሪያ ጥቃቅን አካላትን እንዲሁም የሽንት መውረጃ ቧንቧዎችን የተመለከቱ ጉዳዮች በዝርዝር ይተነተናሉ።
ልባችንና ከእርሷ ጋር የተያያዙት እጅግ በርካታ ደምስሮች በአንድነት ሆነው የሚያዋቅሩት ስልት ስልተ ልብደምስር ይባላል። እዚህ በሰፊው ይብራራል።
ይህ ቦታ የዎንዶች እና የሴቶች የመራቢያ አካላት በመዝርዝር የሚጠኑበት ክፍል ነው።
ስልተ መብለልት የተመገብነው ምግብ የሚብላላበትና ወደ አካል የሚሰርጽበት ስልት ነው። እዚህ ስልተ መብለልትን የተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች ይቀርባሉ።
በአካል ውስጥ የሚዘዋወር ደም ያልሆነ ፈሳሽ አለ። ያ ፈሳሽ ጠንበል (lymph) ይባላል። ይህ ስልት በምን መልክ እንደተዋቀረ በዚህ ስፍራ ላይ ተብራርቶ ይቀርባል።
ማውጫ/Contents
አሁንም አሁንም አየር እያስገባን የምናስወጣው በስልተ እስትንፋሳችን ነው። ይህን ስልት ለመረዳት የሚረዱ ትንታኔዎችን ጋብዘንዎታል።
ሰውነት በየቀኑ ያላስተዋልናቸውንና ያስተዋልናቸውን ጉዳቶች እያስተናገደ ይውላል ሆኖም ራሱን የሚጠግንበት ስልት አለው እሱም ስልተ ፈውስ ይባላል።
ሰዘውነታችን ተጥመልማይ ተዘርጋፊ የስጋ ክምር ወይም ጥቅል ያልሆነው በውስጡ ልዩ ልዩ አይነት አጥንቶችን በመያዙ ነው። አጥንቶችን አቀናብሮ የያዘው የአካል ስልት ስልተ አጽም ይባላላል። እዚህ በሰፊው ይብራራል።
የውስጥና የውጭ አካላትን የሚሸፍኑ የሰውነት ክፍሎችን ያጠቃልላል። ከሁሉ ትልቁ የአካል ክፍል የሆነው ቆዳችን በዚህ ስልት ስር ይጠቃለላል።
አካል ከስፍራ ስፍራ እንዲንቀሳቀስ፤ አፍ እንዲያላምጥ፣ ክንድ እንዲዘረጋና እንዲታጠፍእንዲታጠፍ፤ ልብ እንድትመታ እና ጨጓራ እንዲፈጭ ለሁሉም እንቅስቃሴ የተለያዩ አይነት ጡንቻዎች ያስፈልጋሉያስፈልጋሉ። እነዚህን የያዘው ስልት ስልተ ጡንቻ ይባላል።
የሰውነታችንን አፍላቂ እጢዎችና የሚያመነጯቸውን ር እሰ ቅመሞች አጠቃሎ የያዘ የአካል ክፍሎቻችን ተግባራቶቻቸውን በአስፈላጊው ወቅት እንዲሰሩ የሚያግዝ ስልት ነው፡፡
ስለተ መቅመምት/endocrine system